Popular Posts

Friday, December 19, 2014

Dunguza belongs to Gamo

Gamo Dunguza

 Dunguza Belongs to Gamo!


 Dunguzay nuoyissa!”





Monday, December 8, 2014

የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድና ዲኤምሲ

የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድና ዲኤምሲ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ለሁለት ቀናት ተቀብላ ያስተናገደችው አርባ ምንጭ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን ወደ ቤትዎ በሰላም መጡ››፣ ‹‹እንኳን ለከተማችን 50ኛ ዓመት አደረሰን›› የሚሉና የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ባነሮች በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ተሰቅለው ይታያሉ፡፡

ከተቆረቆረች ግማሽ ምዕታመት ያስቆጠረችው አርባ ምንጭ የ50ኛ ዓመት የልደት በዓልዋን በተለያዩ ክንውኖች ያከበረች ሲሆን፣ የበዓሉ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ደግሞ ባለፈው ነሐሴ 30 ቀንና ቅዳሜ ጳጉሜን 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ተከናውኗል፡፡

ከበዓሉ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም መካከል አንዱ አርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን የተገነባውና የአርባ ምንጭ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታን ያጠቃለለው የሁምቦ አርባ ምንጭ የምዕራፍ አንድ 75 ኪሎ ሜትር መንገድ የምረቃ ሥርዓት ነው፡፡

ለአርባ ምንጭና ለአካባቢው ነዋሪዎች የዓመታት ምኞት የነበረው ይህ የመንገድ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በይፋ ተመርቋል፡፡ መንገዱ ለዚህ ደረጃ መብቃቱ ለከተማው ነዋሪ የተለየ ስሜት የፈጠረ ነበር፡፡ ደስታቸውንም በአደባባይ ወጥተው ገልጿል፡፡ ወደ አርባ ምንጭ ለመግባት ወይም ከአርባ ምንጭ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ለመጓጓዝ እርጅና የተጫነው ከርካሳ መንገድና በኩልፎ ወንዝ ላይ የነበረው ድልድይ ከተማዋን ከአጠቃላይ እንቅስቃሴ የገታ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እንደገለጸው፣ አሁን በአስፓልት ደረጃ የተሠራው መንገድ ከ45 ዓመት በፊት በጠጠር የተሠራ መንገድ ሲሆን በአገልግሎት ብዛት ተጎድቶ የቆየ ነው፡፡ አርባ ምንጭ ከተቆረቆረች ከሦስት ዓመት በኋላ ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ሆነው የቆዩት አቶ ዘውዱ ጥላሁን እንደሚሉት፣ በኩልፎ ወንዝ ለመሻገር የነበረው ፈተና ቀላል አልነበረም፡፡ በመንገዱ መጎዳት ምክንያት ተሽከርካሪዎች ወደዚህ አካባቢ እንደልብ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ በዕለቱ የተመረቀው የ75 ኪሎ ሜትር መንገድ ከመሠራቱ በፊትም የነበረው መንገድ አርባ ምንጭን ወደኋላ ያስቀረ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘውዱ፣ ይህ ታሪክ የሚለወጥ ስለመሆኑ ይናገራሉ፡፡

የዚህ መንገድ ግንባታ መጠናቀቅ የተለየ ስሜት እንዳሳደረባቸው ከገለጹት መካከል አንዱ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ናቸው፡፡ በምርቃት ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹትም፣ ‹‹የከተማዋን 50ኛ ዓመት እያከበርን ባለንበት ወቅት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ የከተማችን ቁልፍ ችግር የሆነውን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በመፈጸም በአርባ ምንጭ ከተማ ታሪክ በአጭር ጊዜ ትልቅ ድልድይ ተገንብቶ ተረክበናል፡፡ ከተማዋን ለሁለት የከፈለውን ወንዝ በማገናኘት በይፋ የተመረቀውን ድልድይ የከተማችን የልደት በዓልዋ ስጦታ አድርገን የምንወስደውም ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የከተማዋን አስፓልት ሥራ ሌት ተቀን በመሠራታቸው የዲኤምሲን ባለቤት አቶ ዳንኤል ማሞን፣ የኩባንያውን ሠራተኞችና አማካሪ መሀንዲስን አመስግነዋል፡፡

በዲኤምኤስ ኮንስትራክሽን የተገነባው ይህ መንገድ በከተሞች አካባቢ 27 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአነስተኛ ከተሞች ደግሞ 19 ሜትር ስፋት ኖሮት የተሠራ ነው፡፡ ከ825.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪም ጠይቋል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ የተጀመረው በብላቴ ወንዝ ድልድይ ሲሆን፣ በአርባ ምንጭ ከተማ በምትገኘው በኩልፎ ወንዝ ድልድይ የሚያበቃ ነው፡፡ የኩልፎ ወንዝ ድልድይም 62 ሜትር ርዝመትና 28.6 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰቀላንና የሰቻ ከተሞችን ያገናኛል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ የሦስት አደባባዮች ግንባታም የዚሁ ፕሮጀክት አካሎች ናቸው፡፡

የዚህ መንገድ ግንባታ ለዚህ ደረጃ ይብቃ እንጂ መንገዱ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ያለመጠናቀቁ የአካባቢውን ነዋሪዎች ያስቆጣ ነበር፡፡ አቶ ዘውዱ እንደገለጹትም፣ የመንገዱ የግንባታ ሥራ በመሀል ላይ መቋረጡ የከተማውን ነዋሪ ተስፋ እስከማስቆረጥና ለአቤቱታም ወደ መንግሥት አካላት ቀርቦ ነበር፡፡ አሁን ግን ያ ሥጋት ቀርቶ አያልቅ ይሆን ተብሎ የነበረው መንገድ ቃል በተገባው መሠረት እውን መሆኑ እርሳቸውንም ሆነ የከተማዋን ነዋሪ አስደስቷል ብለዋል፡፡ በተለይ መንገዱ ለምን እንደተጓተተ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና ከአስተዳደሩ ከተሰጠው ማብራሪያ ሌላ ኮንትራክተሩ መንገዱን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀው እንደሚያስረክቡ በገቡት ቃል መሠረት መፈጸማቸው እጅግ ያስደሰታቸው ስለመሆኑም አቶ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡ ከዋናው መንገድ ሌላ የከተማው የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ በተገባው ቃል መሠረት ተሠርቷል፡፡ ጥቃቅን የሚባል ቀሪ ሥራዎችንም ለማጠናቀቅ ቀን ተሌት እየተሠራ ሲሆን፣ የመንገዱ ግንባታው የከተማዋን ገጽታ መቀየር ችሏል፡፡

ዲኤምሲ የዚህን መንገድ ፕሮጀክት ሲረከብ የፕሮጀክቱ ግንባታ 106 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ቢኖረውም፣ በዕለቱ ግንባታው ተጠናቅቆ የተመረቀው ግን 75 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ቀሪው 31 ኪሎ ሜትር መንገድ ለብቻው ተነጥሎ እንደ አዲስ ፕሮጀክት እንዲሠራ ተደርጓል፡፡ ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት ነበረው፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹትም፣ ለመንገድ ፕሮጀክቱ መዘግየት ዋነኛ ተደርጎ የተወሰደው በግንባታ ወቅት በፕሮጀክቱ የተለያዩ ቦታዎች ያጋጠሙ ችግሮችና በጥቅሉ 31 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የፕሮጀክቱ ክፍል እንደ አዲስ መሠራት ስለነበረበት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደገለጹትም፣ 31 ኪሎ ሜትሩ መንገድ ችግር የፈጠረው ቀደም ብሎ በተሠራው ዲዛይንና የግንባታ ደረጃ ሊሠራ ባለመቻሉና የዲዛይን ለውጥ በማስፈለጉ ነው፡፡ አጠቃላይ የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጠናቀቅ የነበረበት በ2004 ዓ.ም. ነበር፡፡ ሆኖም በግንባታ ወቅት በተለያየ ቦታ 31 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ዲዛይን እንደገና እንዲሠራ ማስገደዱ ደግሞ የፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ እንዲቋረጥ እስከማድረስ ደርሶ ነበር፡፡ ለፕሮጀክቱም ሥራ ትልቅ ፈተና ነበር፡፡ ይህ ክፍል ተነጥሎ እንዲወጣ ተደርጎ ቀሪው 75 ኪሎ ሜትር መንገዱ እንደ ምዕራፍ አንድ ሥራ ተወስዶ ቀሪው 31 ኪሎ ሜትር መንገድ ደግሞ እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮጀክት ተወስዶ እንዲሠራ ሊወሰን ችሏል፡፡ በዚህ ውሳኔ መሠረት አዲስ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ በዚህም ጨረታ ዲኤምሲ አሸናፊ ሆኖ ሥራውን ተረክቦ ግንባታውን በማከናወን ላይ ነው፡፡

እንደ አቶ ሳምሶን ገለጻ በዚህ ጨረታ አምስት ተቋራጮች ተወዳድረው ነበር፡፡ እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ ለተቆጠረው ለ31 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በወጣው ጨረታ ዲኤምሲ አሸናፊ የሆነበት ዋጋ በ700.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ በአዲሱ ውል መሠረት የሁለተኛው ምዕራፍ መንገድ ግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከ2007 ዓ.ም. አጋማሽ በኋላ ይሆናል ተብሏል፡፡

የሁምቦ አርባ ምንጭ አስፋልት መንገድ የሁለተኛው ምዕራፍ 31 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ ርዝመታቸው እስከ 80 ሜትርና 19 ሜትር ስፋት ያላቸው የሁለት ትላልቅ ድልድዮች ግንባታ ሥራዎችን አካቶ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመንገዱ ግንባታ ከ51 በመቶ በላይ የተከናወነ ሲሆን፣ 130 የሚሆኑ የውኃ መተላለፊያ መስመሮች ግንባታን በማካተት የአዲስ ቴክኖሎጂና አሠራር ዘዴንም በመጠቀም ግንባታው እየተፋጠነና በሚቀጥሉት ጥቂት ወራትም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለዚህ በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው መንገድም ከ700.4 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግሥት ተመድቧል፡፡

የ75 ኪሎ ሜትር መንገድ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ የዚህ መንገድ ግንባታ መጠናቀቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አለው፡፡ ‹‹የአርባ ምንጭና አካባቢው በአገሪቱ ትልቅ ሀብት ያለበት ተብሎ የሚወሰድ ቦታ ነው፡፡ የቱሪዝም ሀብቱ ተዝቆ የማያልቅ ነው፡፡ ስለዚህ ቱሪስቶች በሰላምና በተመቻቸ ሁኔታ እንዲጓዙ ካስፈለገ መሠረተ ልማት በጣም ወሳኝ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የአርባ ምንጭ አካባቢ በፌዴራል መንግሥት የሆርቲካልቸር ክላስተር ተብሎ የተመረጠ በመሆኑ ወደፊት የአግሮ ፕሮስሲንግና አበባን ጨምሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የሚካሄዱበት አካባቢ እንደሚሆን የጠቀሱት አቶ ኃይለ ማርያም፣ እንዲህ ዓይነቱን ዕቅድ ለማስፈጸም እንዲህ ዓይነት መሠረተ ልማቶች የግድ ማስፈለጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ የአውሮፕላን ማረፊያን መሠረት አድርጎ በቀጥታ ዓለም አቀፍ በረራ የሚኖርበት ዕድል ስለመኖሩም የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ባለሀብቶች እዚህ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ካስፈለገ መሠረተ ልማት የግድ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹አርባ ምንጭ ከፍተኛ የሙዝ ምርት በማምረት የሚታወቅ ነው፡፡ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሙዝ ከአርባ ምንጭ ይጫናል፡፡ ለዚህ ምርት የሚሆን የተሻለ መንገድ መኖር ስላለበት እንዲሁም ለአጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚ ልማት አሁን የተሠራው መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፤›› ብለዋል፡፡ በዕለቱ የተመረቀው መንገድ የቱሪስት መናኸሪያነታችንም ከፍ የሚያደርግ ነውና የመንገድ ግንባታው ተጠናቅቆ ሥራ መጀመሩ በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ የተቋራጮች የብቃት ደረጃን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ ‹‹የአገራችን ተቋራጮች በኮንክሪት አስፓልት መንገድ ላይ የተሻለ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹በእርግጥ በየጊዜው ውጣ ውረዶች አሉ፡፡ አሁን እንደሚታየው ጠንክረው ከወጡ ወደፊት የአገሪቱን የመሠረተ ልማት ግንባታና ትልልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችንም ጭምር አገራዊ ተቋራጮች ሊይዙ እንደሚችሉ በትክክል ምልክቶች እየታዩ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ግን መንግሥትም ደግፏቸው አቅማቸው የበለጠ መጎልበት እንዲችል ማድረግ አለብን ያሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ አሁንም ቢሆን ግን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዕውቀት ችግርን አልተሻገሩም ብለዋል፡፡ ስለዚህ መኩራራት እንደማያስፈልግና የዓለምን የመጨረሻ እስክንደርስ ድረስ መሻሻሎች መኖር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የአገር በቀል ኮንትራክተሮች ጥሩ እየሄዱ ቢሆንም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንቱ መሻሻል ይኖርበታል፡፡ የሁምቦ አርባ ምንጭም ፕሮጀክት ከጊዜ አንፃር ሲታይ የተወሰነ መዘግየት መታየቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንዲህ ዓይነት መዘግየቶች በማስወገድ አቅማቸውን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል፡፡ ‹‹አሁን ኮንትራክተሩ (ዲኤምሲ) ራሱን አሻሽሎ ሪስትራክቸር አድርጎ በመግባቱ የተሻለ ሥራ ሠርቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ተምሮ ሌሎችም ኮንትራክተሮች የበለጠ ውስጣቸውን እንዲፈትሹ መንግሥትም የአቅም ግንባታ ሥራን ማጠናከር ይገባናል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው ደግሞ የመንገድ ፕሮጀክቱ በቱሪስት መስህብነት የምትታወቀውን የአርባ ምንጭ ከተማን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በደቡብ ክልል የሚገኙ ሦስት ዞኖችንና አንድ ልዩ ወረዳን ማለትም የከምባታ ጠምባሮ፣ የጋሞ ጎፋና የወላይታ ዞኖችንና የአላባ ልዩ ወረዳን እርስ በርስ የሚያገናኝ ጭምር ነው፡፡ መንገዱ ከሞጆ ተገንጥሎ እስከ ጎረቤት አገር ኬንያ ድረስ የሚዘልቅ ዋና መንገድ አካል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያን ክፍል ከሌሎች ጋር ለማገናኘትና ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑን የሚገልጸው የባለሥልጣኑ መረጃ ይህም ጊዜን፣ ገንዘብንና እንግልትን በእጅጉ እንዲቀንስ ያስችላል ብሏል፡፡
10 September 2014 ተጻፈ በ ዳዊት ታዬ[reporter ጋዜጣ]

'በአርባ ምንጭ ከ875 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሪፈራል ሆስፒታል ሊገነባ ነው!"

 በአርባ ምንጭ ከ875 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሪፈራል ሆስፒታል
ሊገነባ ነው!"(By kirubel habtemariam in Arba minch)
  የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሚያስገነባው የሪፈራል ሆስፒታል እና የመማርያ ህንፃ “ይርጋለም ኮንስትራክሽን” ከተባለው የህንፃ ተቋራጭ ድርጅት ጋር ስምምነት ፈፅሟል።በደቡብ ክልል አሉ የሚባሉትን የዲላ እና የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታሎችን “ያስንቃል” የተባለለት ይህ የአምዩ የጤና ሳይንስ እና የህክምና የመማርያ ሪፈራል ሆስፒታል ህንፃ “መድሀኒያለም ቤተክርስትያን” አካባቢ ከዋናው አስፓልት መንገድ ዳርቻ እንደምያርፍ ለማወቅ ተችሏል።ስምምነቱ በተደረገ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ የሚገባው እና በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቀው የዚህ ሪፈራል ሆስፒታል ህንፃ ለአርባ ምንጭ ከተማ ትልቅ ውበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አጌና አንጂሎ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የሚያስገነባው የሪፈራል ሆስፒታል በሀገሪቱ በጤና ትምህርት መስክ የሚታወቁት የጎንደር እና ጂማ ዩንቨርሲቲዎች ካስገነቧቸው የሪፈራል ሆስፒታሎች ጋር የሚወዳደር እንደሆነ መናገራቸውን የዩኒቨርሲቲው ድህረ-ገፅ አስነብቧል።
(Gamo Dunguza,an identity of the Gamo people in southern Ethiopia!)

AMU, Yirgalem Construction sign pact to build Specialty Hospital

Arba Minch University today has entered into an agreement with the Hawassa-based Yirgalem Construction plc to build 300-bedded Teaching-cum-Referral hospital near Madhanalem Church at Arba Minch on 5.1 hectares of land, informed Academic Affairs Vice President, Dr Agena Anjulo.

Dr Agena Anjulo from AMU and Engineer Mr Zelalem Woldemariam, who is Manager with the Yirgalem Construction, signed the pact in the presence of AMU top officials at Senate Hall on Oct 3, 2014. The construction would start after 21 days from now and likely to take 900 days to complete.
‘‘This hospital will be unique of its kinds because the general hospital built in 1950 at Arba Minch alone has been carrying the burden. It will not only train medical students, professionals but the entire community would get benefit. Its infrastructure, technical knowhow and expertise would surpass the hospitals built in Hawassa and Dilla,’’ Dr Agena claimed.

The construction would incur ETB 875 million and likely to be completed within three years time. It would have key clinical departments i.e. orthopedic, obstetrics, cardiology intensive care unit, pediatrics, neonatal, cardiovascular, gynecology, ophthalmology, surgery, nursing etc.
This would be one of the landmark institutions in South Nations and Nationalities People’s Region as it would render specialized medical treatment to the community, which till date was a far cry. It would end the anxiety of common man getting frenetic when afflicted by the disease which could only be treated in Hawassa or Addis Ababa, but now scenario would be different.
Dr Agena was very appreciative of Zonal and City Administration for providing 5.1 hectares of land to university for the hospital. College of Medicine & Health Sciences Dean Mr Behailu Medikios, said, ‘‘Apart from students education, we would also give training in specialized areas to churn out professionals in line with the needs and requirement of the nation.’’
By Philips Joseph



Friday, December 5, 2014

"አርባ ምንጭ የባከነ ጊዜዋን እያሰላች ለቀጣይ ስኬት መንደርደር ጀምራለች"

 



  "አርባ ምንጭ የባከነ ጊዜዋን እያሰላች ለቀጣይ ስኬት መንደርደር ጀምራለች"
 የከተማው መግቢያ በር አካባቢ አሁንም በግንባታ ማሽኖች ድምፅ እንደታጀበ ነው፡፡ ነዋሪውን ካማረሩ ጉዳዮች መካከል የዚህ መንገድ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቅ አንዱ ነው፡፡ ከተጀመረ ሰባት ዓመት ያለፈው የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድ እስከ አሁን አለመጠናቀቁን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ሳይቀሩ ይደነቁበታል፡፡ ወጣት በኃይሉ ከነዚህ የቀድሞ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በአርክቴክት ሙያ የተመረቀው በኃይሉ የመንገዱን አለመጠናቀቅ ሲሰማ አሁንም ድረስ ይገርመዋል፡፡ ገና ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመድበው ሲሄዱ ጀምሮ እስከ ምርቃት ቀን ድረሰ የሁምቦ አርባ ምንጭ ጎዳና በከባድ አቧራ መታፈኑን በመሰልቸት ያስታውሳል፡፡ የወጣት አርክቴክት ሃሳብ ብዙዎች ይጋሩታል፡፡
መንገዱ አሁንም በብዙ ውጣ ውረዶች ታጅቦ፤ ሲጀመር ተይዞለት ከነበረው 340 ሚሊዮን ብር በጀት ወደ700 ሚሊዮን ብር በላይ ልቆ በቀጣዩ ዓመት መግቢያ ወራት ሊጠናቀቅ ተስፋ ተደርጎበታል፡፡ የጎልማሳነት ዕድሜዋ ላይ የምትገኘው አርባ ምንጭ ከታደለችው የተፈጥሮ ሀብት ተገቢውን ጥቅም እንዳታገኝ የመንገዱ አለመጠናቀቅ የኋሊት መጎተቱ እሙን ነው፡፡ በቅርቡ ሃምሳኛ ዓመት የምስረታ ሻማዋን ለመለኮስ የበቃችው ከተማ «ከዕድሜዋ ጋር የሚመጥን ደረጃ ላይ አትገኝም» ብሎ ለመደምደም ቢከብድም የሚገባት የዕድገት ደረጃ ላይ ላለመሆኗ ማሳያዎች ብዙ ናቸው፡፡ ለምስረታዋ ሃምሳኛ ዓመት መከበር ምክንያት ከሆኑት መካከልም ባለፉት ዘመናት አንዴ ሞቅ ከዚያ ደግሞ ቀዝቀዝ የሚለውን የለውጥ ሂደት ወጥ በሆነ መልኩ የዕድገት ሀዲድ እንድትጓዝ ነው፡፡
የበዓሉን መቃረብ አስመልክቶ በከተማዋ የነበረን ቅኝት በነዋሪው ምልከታ እና ትዝብት የታጀበ ነበር፡፡ ሁሉም ነዋሪ ከተማዋን በሚያይበት የራሱ መነፀር ባለፉት ዓመታት «ይሄ ለውጥ አለ» በቀጣይ ደግሞ «መለወጥ አለበት» ያሉትን አውግተውናል፡፡ ከከተማው አንደኛው ክፍል በተለምዶ ሴቻ ከሚባለው አካባቢ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ጎርፉ ከተማዋ ባለፉት ጊዜያት የሚጠበቅባትን ያህል በዕድገት መራመድ ባትችልም በተለይ ከሁለት ዓመታት ወዲህ መነቃቃት ታይቶባታል፡፡ የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መገንባት ለለውጡ አንድ ማሳያ አድርጎ ያነሳዋል፡፡ ነገር ግን ነዋሪው በከተማው ልማትም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያሳየውን ቸልተኝነት መታዘቡን ይጠቅሳል፡፡
ልማቱ በህዘቡ ሙሉ ተሳትፎ ማደግ እንዳለበት የሚያምነው ወጣት ዳንኤል «በልማት ዙሪያ ነዋሪው በጋራ መወያየት እና መስራትን ባህሉ ማደግ ይገባዋል» የሚል ሃሳብ ያንፀባርቃል፡፡ በተጨማሪም በከተማው በጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው በሚገኙ ወጣቶች ላይ የታዘበውን ጉዳይ ይናገራል፡፡ በርካታ ወጣቶች ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ መኖራቸውን፤ ነገር ግን እነዚህ ወጣቶች ላይ ደካማ የቁጠባ ባህል ማስተዋሉን ያነሳል፡፡ ከወጣቶቹ በተጨማሪ ማህበራቱን በሚያደራጁት አካላት ላይ «የክትትል ማነስ ይታያል» ይላል፡፡ በቀጣይ ግን ራሱም የመደራጀት ፍላጎት እንዳለው በመጥቀስ አስተያየቱን ይቋጫል፡፡
በዚሁ አካባቢ ያነጋገርኳት ወጣት ደግሞ በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራች ናት፡፡ የቤተሰቧን ሆቴል በማስተዳደር ላይ የምትገኘው ወጣት ስሟን ከመግለፅ እንድቆጠብ ጠየቀችኝ፡፡ እንደ ፍላጎትሽ ይሁን ብዬ ወጋችንን ጀመርን፡፡ ወጣቷ በከተማው ውስጥ በርካታ ለውጦች ያስፈልጋሉ ትላለች፡፡ ለሃሳቧ መነሻ ያደረገችው ደግሞ ወደ ከተማዋ የሚያደርሰው መንገድ ለረጅም ጊዜ ተጓትቶ እስከ አሁን አለመጠናቀቁን ነው፡፡ በተጨማሪም በንግድ ቤቶች፣ በትራንስፖርት ዘርፍ ችግሮች መኖራቸውን ትናገራለች፡፡ በንግድ ቤት ላይ የሚቀመጠው ግምታዊ ግብር ለነጋዴው አለመመቸቱን ታስረዳለች፡፡ በዚህ ምክንያት ነጋዴው ዘርፍ በመቀየር ላይ መሆኑን ጠቁማለች፡፡
ወጣቷ በከተማው ባላት ቆይታ ካየቻቸው በጎ መሻሻሎች መካከል አርባ ምንጭን አቋርጦ የሚያልፈውን መንገድ ነው፡፡ እንዲሁም በአገሪቱ በተለይ በውሃ ዘርፍ ገናና የሆነው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መስፋፋት ታነሳላች፡፡ ይሄም በዘላቂነት ትኩረት ተሰጥቶት ሊቀጥል ይገባል ባይ ነች፡፡ በነጋዴው ላይ ከግብር ጋር ተያይዞ የሚያጋጥመው ችግር መቀረፍ እንዳለበት ሃሳቧን ሰጥታለች፡፡ «በውሃ እና መብራት ላይ የሚታዩ መቆራረጦች ተደጋግመው ይታያሉ» የምትለው ወጣቷ፤ እንደሌሎቹ የከተማዋ ችግሮች ሁሉ በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም የሚታዩ ክፍተቶች መኖራቸውን አስረድታለች፡፡ በተረፈ ግን የቱሪስት መዳረሻ የሆነችው ከተማ ከዘርፉ ይበልጥ እንድትጠቀም በፀጥታና ተያያዥ ችግሮች ላይ ዘላቂ መፍትሄ ሊመጣ ይገባል ትላለች፡፡
የዕድሜ ባለፀጋው አቶ ዋጌሾ ዋዛ የአርባ ምንጭ ከተማ አስራ አምስት ዓመት ታላቅ ናቸው፡፡ በዚህ ቆይታቸው ብዙ ነገር ታዝበዋል፡፡ ከተማዋ ጫካ ከነበረች ጊዜ አንስቶ በደንብ ያውቋታል፡፡ ታዲያ አሁን ያለው የከተማ ዕድገት፣ የመሰረተ ልማት መስፋፋት በግልፅ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች መሰል ከተሞች ጋር ሲያወዳድሯት ለእርሳቸው አርባ ምንጭ አሁንም ብዙ ይቀራታል፡፡ «ድሮ እንድ እቃ አስር ብር ከገዛክ መርፌ ምርቃት ነበር፤ አሁን መርፌ በአቅሙ ተወዷል» የሚሉት አቶ ዋጌሾ፤ የኑሮ ውድነት የከተማው ነዋሪ ችግር መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በቀጣይ የዚሁ ኑሮ ውድነት መረጋጋት ምኞታቸው ነው፡፡
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሽመልስ ታደሰ እንደሚሉት አርባ ምንጭ ዛሬ የደረሰችበት ደረጃ የአምሳ ዓመት ውጤት አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡ «ከከተማዋ ምስረታ አንስቶ ባሉት ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ብዙ ለውጥ ሳታሳይ ቆይታለች» የሚሉት ከንቲባው፤ ዛሬ የሚታዩ የመሠረተ ልማትም ሆኑ ሌሎች ግንባታዎች የባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ጥረት ውጤቶች መሆናቸውን ያብራራሉ፡፡ በነዚህ ዓመታት ለውጦቿ በሌሎች ከተሞች እንደሚታየው ፈጣን መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ከተማዋ ከተፈጥሮ መስህቦቿ ከምታገኘው የቱሪስት ገቢ በተጨማሪ በአትክልትና ፍራፍሬ አኮኖሚዋ ማገዝ ችላለች፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለይም የአባያ እና ጫሞ ሃይቅ ዋናው የቱሪስት መዳረሻ ያደርጓታል፡፡
እስከ አሁን አትክልትና ፍራፍሬ በቀጥታ ወደ ገበያ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን እሴት በመጨመር ወደ ገበያ ማቅረብ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ዕድሉ ክፍት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተለይም ከንግዱ ማህበረሰብ የሚነሳው የግብር አሰባሰብ ሂደት ቅሬታ አስመልክቶ የግብር ግምት ትመናው ይበዛብናል የሚል ቅሬታ በተደጋጋሚ እንደሚነሳ አስታውሰው፤ በነጋዴው ዘንድ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ ላለመሆን መፈለግ ስለሚስተዋል ይሄን ከማስተካከል ጋር የተያያዘ ነው፡፡ «የግብር ተመን በዛብን» የሚሉት ግን በግብር ሕጉ መሰረት ይግባኝ ማለት እንደሚቻል አንስተዋል፡፡ የከተማዋን ከንቲባ በአባልነት የያዘ የነጋዴ ቅሬታ በአግባቡ የሚመለከት ኮሚቴም መቋቋሙንም አስረድተዋል፡፡
በከተማዋ ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት አስር ወራት ከ17 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን በማንሳት፡፡ በዚህም ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ዕድል የተመቻቸ ሲሆን ዘርፎቹም በማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ አገልግሎት እና ንግድ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በኮብልስቶን ንጣፍ በደቡብ ኦሞ ስኳር ልማት፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያዎች ላይ የተሳተፉ አሉ፡፡ በቀጣይም ይሄ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው በከተማዋ የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም እና የኮንፍረንስ ማዕከል መሆኗን ይበልጥ ለማስተዋወቅ በቀጣይ ብዙ ይሰራል፡፡ ሃምሳኛ ዓመት በሚከበርበት ወቅት በዋናነት ለቀጣይ ስኬቶች መሰረት የሚጥሉ ተግባራት ይከናወንበታል፤ ከኢንቨስትመንቱ ባሻገር መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡ በቱሪዝም፣ ግብርና እና ኢንዱስትሪ ላይ በርካታ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባም ጠቁመው፤ በኢንቨስትመንት በኩል እንደ ዞን በተለይም የቆላ እና የደጋ ፍራፍሬዎች ላይ ዕሴት ጨምሮ ወደ ገበያ ማድረስ አሁንም ትኩረት ይፈልጋል፡፡
በከተማዋ ህዝብ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጨምር የመንገድ ፍላጎት መኖሩን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ ከመንገድ በተጨማሪ የውሃ እና የመብራት ፍላጎትም አድጓል፡፡ የነዋሪውን ፍላጎት ለሟሟላትም ከተማዋን አቋርጦ ከሚያልፈው ዋና መንገድ በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ ግንባታዎች በመከናወን ላይ ቢገኙም፤ «ከከተማው አቀማመጥ ጋር ተያይዞ ግንባታዎቹ ፈታኝ ሆነው ቆይተዋል» ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚያሰራው የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድ ግንባታ ከረጅም መጓተት በኋላ በተሰጠው ትኩረት በ2007 ዓ.ም መግቢያ ላይ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ይበቃል፡፡
የከተማዋ ከፍተኛ ችግር ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነውን የድልድይ እጥረት ለመቅረፍ የተለያዩ ድልድዮች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ከተማዋ በበርካታ ሸለቆዎች ውስጥ እንደመገኘቷ እስካሁን ህዝብን ከህዝብ ለማገናኘት አስቸጋሪ የነበሩ አካባቢዎች በድልድይ እንዲገናኙ እየተደረገ ነው፡፡ ከፍሳሽ ማስወገድ ጋር በተያያዘ በከተማ ውስጥ 25 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ግንባታ ተከናውኗል፡፡ የንፁህ መጠጥ ውሃ በተመለከተ ለቀጣይ አርባ ዓመት ችግሩን ሊቀርፍ የሚችል ፕሮጀክት በበዓሉ ወቅት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
አርባ ምንጭ ከተመሰረተች ሃምሳ ዓመት ቢሆናትም የከተማ መዋቅር የያዘችው በ1995 ዓ.ም የከተማ ልማት ፖሊሲ ሲተገበር ነው፡፡ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታገሰ ጨፎ ባለፉት አስር ዓመታት በከተማዋ ዕድገት ላይ ረጅም ርቀት መሄድ ተችሏል ብለዋል፡፡ በመሰረተ ልማት እና በማህበራዊ አገልግሎት ተጨባጭ ለውጥ ታይቷል፡፡ ከተማዋ ለባለሀብቱ ምቹ መሆኗን አስመልክቶ «በትንሽ ጥረት ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚቻልባት» ሲሉ ይገልጿታል፡፡ እንደርሳቸው አሁን ያለው ፈጣን ዕድገት ይዞ መጓዝ ከተቻለ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የተመዘገበውን ልማት በቀጣዮቹ 15 ዓመታት ለማምጣት የሚያስችል መሰረት መጣሉን ነው፡፡
የሆነው ሆኖ አርባ ምንጭ ያለፉ ዘመኖቿን በቁጭት እያሰበች ለወደፊት ስኬት ሞራል ሰንቃለች፡፡ ከተማዋን ከሁለት የባህር ማዶ ከተሞች ጋር በእህትማማች ከተማ የማስተሳሰር ስራ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ ገልጸዋል፡፡ ከአምሳ ዓመት በፊት በወቅቱ አካባቢውን ያስተዳድሩ የነበሩ አዕምሮ ሥላሴ የተባሉ ሰው ከጨንቻ ወደ ጊዶሌ ሲሄዱ በማየታቸው አካባቢው የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ እንድትሆን መምረጣቸውን ከንቲባው ነግረውናል፡፡ ከተማዋ በተፈጥሮ ሀብቶቿ በተለይም በአባያ እና ጫሞ ሃይቆች የምትታወቅ ሲሆን ነዋሪዎቿም አስክ 103 ሺ ይገመታል፡፡
Details
Published Date
Written by ብሩክ በርሄ
Category: ፖለቲካ
Add comment

Thursday, December 4, 2014

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት/ኢዜአ/ በዘገባው በሀገሪቱ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ ከተሞች መካከል የአርባ ምንጭ ከተማ አንዷ መሆን ችላለች ሲል ይዘግባል
በፍጥነት እያደጉ ካሉ ከተሞች መካከል አርባምንጭ አንዷ ሆናለች
አርባምንጭ ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ ያላት ከመሆኗም በላይ «በፍጥነት እያደገች የመጣች ከተማ ናት» ሲሉ ብዙዎች እየመሰከሩ ነው፤
በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ ከተሞች መካከል አርባምንጭ አንዷ እየሆነች መምጣቷን መታዘባቸውን አንዳንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተናገሩ።
...
ከተማዋ የተመሰረተችበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን ለማክበር ከተገኙት እንግዶች መካከል አንዳንድ ባለስልጣናት እንዳሉት፤ አርባምንጭ በሁሉም የልማት መስኮች ወደፊት እየተራመደች ያለች ከተማ ሆናለች።
በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የአመራር አቅም ግንባታ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ገዛኽኝ አርባምንጭ በከተማ የባለሀብቶች ጠንካራ ተሳትፎ እየተስተዋለባት ያለች የቱሪስት መዳረሻ እንደሆነች አመልክተዋል።
« አገሪቱ በተከታታይ እያስመዘገበችው ያለው ባለሁለት አሃዝ እድገት በከተሞች እደገት ላይ ውጤቱ እየተንፀባረቀ ነው፤ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአርባምንጭ ከተማ ላይም በግልፅ መስተዋሉን ተናግረዋል።
እየተራመደችበት ያለው የእድገት ግስጋሴ ቀጣይነት እንዲኖረው በተለይ ነዋሪውና የግል ባለሀብቱ በቀጣይ ትልቅ ሃላፊነት የሚጠበቅበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
«ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ ያልነበረባት አርባምንጭ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ እድገቷን አፋጥና ዛሬ ሃምሳኛ ዓመቷን ስታከብር የብዙዎችን ቀልብ መግዛት የቻለች ከተማ ሆናለች» ያሉት ደግሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ምትኩ ካሳ ናቸው።
በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በአሳ ሃብት፣ በቱሪዝም ልማትና ሌሎችም የልማት እንቅስቃሴዎች ተመራጭ የሆነች ከተማ መሆኗንም ታዝቤያለሁ ብለዋል።
የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ያቆብ ያላ በበኩላቸው አርባምንጭ ባለፉት 10 ዓመታት ያሳየችው እድገት ወደኋላ የተጎተተችባቸውን ያለፉት 40 ዓመታት ጉዞ በእጥፍ ሊበልጥ የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል።
«በከተማው ያሉ ተቋማትን ግንባታ ስናይ አጠቃላይ የህዝቡን በንግድ፣ በሌሎች ማህበራዊ ዘርፍ እንቅስቃሴዎች በትምህርት በጤናው አገልግሎት፣ በኢንዱስትሪ ልማቱ እንቅስቃሴ ሲታይ በጣም አመርቂ ጥሩ ጅምር ነው» ብለዋል።
አርባምንጭ ከተማ አሁን የደረሰችበትን እድገት ያደነቁት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው መንግስቴ በበኩላቸው አካባቢው እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት በመሆኑ የከተማዋ እድገት በተሳካ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።
አርባምንጭን ከ16 አመታት በፊት ያውቋት የነበሩት የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዶላ ደግሞ «ፍፁም ተለውጣ፣አምራና ተውባ ስላገኘኋት ተደስቻለሁ» ብለዋል





Wednesday, December 3, 2014

የአርባ ምንጭ ትሪቡን ድረ-ገፅ የመስከረም ወር አጫጭር ወሬዎች

በአርባ ምንጭ ከተማ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የገበያ ማእከል ተገነባ
 አርባምንጭ ህዳር 21/2007 በአርባምንጭ ከተማ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ለአገልግሎት መዘጋጀቱን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታውቋል።
 የገበያ ማእከሉ በአርባምንጭ ከተማ በተበታተነ መንገድ ሲካሄድ የቆየውን የግብይት ስርዓት ወደ ዘመናዊ አሰራር ይቀይራል ተብሏል፡፡
 በአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታምሩ ታደሰ ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የገበያ ማዕከሉ የተገነባው የከተማው መሪ ፕላን በሚፈቅደው መሰረት ለንግድ ማስፋፊያ በተለዩ ሁለት አከባቢዎች ነው።
 በከተማው አሁን በስራ ላይ ያሉት የገበያ ቦታዎች የተበታተኑና ለዘመናዊ ንግድ ስራ የማይመቹ ከመሆናቸውም በላይ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችና ሌሎች ሸቀጦች ተቀላቅሎ የሚገበይበት ነው፡፡
 ይህንን ስርዓት በአዲስ መልክ ለመቀየር ከተማ አስተዳደሩ 344 ሱቆችና 33 ሸዶች ያሉባቸው ሁለት ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ገንብቶ ለአገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
 ገበያ ማዕከሉ በዋናነት የኢንዱስትርና የጨርቃጨርቅ ምርቶችና ሌሎች ሸቀጦች የሚገበያዩበት ነው፡፡
 ከግብይት ሱቆቹ መካከል 144 የሚሆኑት በህጋዊ ጨረታ ለንግዱ ማህበረሰብ እንደሚተላለፉና 200 በላይ ሱቆች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ ለተደራጁ ማህበራት በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚቀርብላቸውም ገልጸዋል።
 በነባሩ ሼቻና ስቀላ ገበያ ማዕከል የንግድ ስራ ላይ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አንዳንዶቹ የገበያ ማዕከሉ አሁን በከተማው ውስጥ የሚታየውን የተበታተነውን የንግድ ስርዓት ዘመናዊ ከማድረግ አንጻር የተሻለ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
 ከነጋዴዎቹ መካከል አቶ የሱፍ አብዱልአዚዝና ወጣት ማሙዬ ሰይፉ እንደተናገሩት ዘመናዊ የገበያ ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የብዙ ነጋዴዎችን የንግድ ቦታና የቤት መጣበብ ችግር ይፈታል።
 ገበያ ማዕከሉ የተሟላ መሰረተ ልማት ያለው መሆን እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀው የገበያ ማዕከሉ የተገነባበት ቦታ ከተለመደው የግብይት ማዕከል ወጣ ያለ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ የመንገድ፣ መብራት፣ ትራንስፖርትና ውሃ የመሳሰሉ መሠረተ ልማቶችን አስቀድሞ ማመቻቸት እንዳለበት ገልጸዋል።