Popular Posts

Thursday, May 21, 2015

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል ደኢህዴን/ኢህአዴግን ወክለው ለፓርላማ ይወዳደራሉ

በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሀገርአቀፍ ምርጫ በጋሞ ጎፋ ዞን በሚገኙ የምርጫ ክልሎች የገጂው ፓርቲ ዕጩዎች ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር ብርቱ ትግል ያደርጋሉ                                                                               የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል ደኢህዴን/ኢህአዴግን ወክለው ለፓርላማ ይወዳደራሉ            በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር ድኤታ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ መምርያ ሀላፊ የነበሩት አቶ ታገሰ ጫፎ በመጪው እሁድ በሀገሪቱ ታሪክ ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ገጂው ፓርቲን ወክለው በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል የህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤትን ወንበር ለማግኘት ይፎካከራሉ። 
አቶ ታገሰ በዝህ የምርጫ ክልል ድልን የሚቀናጁ ከሆነ እና መንግስትም አብላጫውን ድምፅ በማግኘት ካሸነፈ በአቶ ሀይለማርያም የድህረ-ምርጫ የካቢኔ ሹም ሸረት ውስጥ የሚኒስትርነት ቦታን ሊቆናጠጡ ይችላሉ ተብሏል።ይሄም የሚሆን ከሆነ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የጋሞ ብሄር ተዎላጅ በሀገሪቱ የከፍተኛ የሥልጣን ዕርከን ውስጥ የሚገባ ይሆናል።በተጨማሪም በዚሁ የምርጫ ክልል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ደኢህዴን በመወከል ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ይወዳደራሉ። በዘንድሮው ምርጫ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብዛት ለፉክክር ከቀረቡባቸው የምርጫ አካባቢዎች እና በገጂውም ሆነ በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ አንድ ጠንካራ የፖለቲካ ይዞታ በምትቆጠረው የጋሞ ጎፋ ዞን አጓጊ ፉክክር ይጠበቃል። በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ አንድነት መድረክ /መድረክ/ ለኢህአዴግ መራሹ ገጂ ፓርቲ ትልቅ ፈተና ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። ለአብነት እንኳን ከሰሞኑ የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ አንድነት መድረክ የውጪ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር መራራ ጉዲና ፓርቲያቸው ድል እንደሚቀናጅ ከሚጠብቁት 5 አካባቢዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ዞን አንዷ እንደሆነች ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርባ ምንጭ ትሪቡን ድህረ-ገፅ ዘጋቢ አንዳንድ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሮ በላከልን ዘገባ መሠረት ምርጫው ሠላማዊ እና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።  በምርጫው ዋዜማ ለከተማዋ ህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበው በተገዙ ሁለት የከተማ አውቶቢሶች መደሰታቸውንም ተናግረዋል። ይሁንእና ግን በርካታ የባጃጅ ሹፌሮች ከሰሞኑ ተገዝተው በመጡት ሁለት የቢሾፍቱ ባሶች ከገበያ ውጪ እንሆናለን በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment