ይድረስ እጅግ ለምወድሽ ውቧ የትውልድ ሀገሬ አርባ ምንጭ!
ከተለያየንበት ግዜ አንስቶ ውዴ ለጤናሽ እንደምን አለሽ?እኔ ካንቺ ሀሳብ በቀር እግዝያር ይመስገን ደህና ነኝ።
በማይነጥፈው የተፈጥሮ ሠገነት ላይ አንቀባረሽ ያሳደግሽኝ የኔ ብሩክታዊት ምዕድር አርባ ምንጭ ሆይ! ዛሬ ይህንን ደብዳቤ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጉዳይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስላንቺ እየሰማሁት ያለው ነገር ነው። ከድንቅ የተፈጥሮ ሀብትሽ እኩል ያንቺ መገለጫ ሆኖ ለበርካታ ዓመታት የቆየው ያ ያንቺ ዘገምተኛ ዕድገት ዛሬ ላይ እየተለወጠ እና ስምሽም ልማት፣ለውጥ፣ግንባታ ወዘተ ከሚሉት ቃላትጋር አብሮ ሲጠቀስ እሰማለው። እኔ ግን ይሄን በአካል ወደ አንቺ ምጥቼ እስከማይ እና እስከምመሰክር ድረስ ካንቺ ማረጋገጥ ፈለኩ።
የምር ግን አርባ ምንጭ እንደሚባለው በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙት የሀገሪቱ ከተሞች ተርታ መሰለፍ ችለሻል? በሁሉም ያንቺ ተዎላጅ ልጆችሽ ዕውቅና እና ምስክርነት የተቸረው ለውጥ ላይ ነሽ? ከሆነ ጥሩ! ሁላችንም የምንፈልገው ያንቺን ዓለም ማየት ነው።
ግን ብቻ ለውጥ እና ዕድገቱ ገጂዎችሽ ለብቻቸው የሚያቀነቅኑት የምርጫ ዋዜማ ነጠላ ዜማቸው እንዳይሆን እናቴ ልብ በይልኝ!
ፈጣሪ ከሌላው ለየት አድርጎ ያጎናፀፈሽ ዕልፍ_አላፍ ተፈጥሮሽ ከዛሬ ነገ ጥቅም ላይ ውሎ አንቺም ተጠቅመሽ ነዋሪዎችሽንም ትጠቅምያቸዋለሽ ስንል በተስፋ በርካታ ዓመታትን ኑረናል።
በፍራፍሬ በተለይም በሙዝ ቅርጫትነትሽ ድፍን ሀገር እንደምትመግቢ ከዚህ አልፎ ተርፎም ባህር ተሻግሮ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ EXPORT መደረግ እንደተጀመረም ይታወቃል። ግን እኔ የምልሽ አርባ ምንጭዬ፤ስሞትልሽ ንገሪኚ፦እንድያው ግን ነዋሪዎችሽ ሙዝ ጠግበው ይበላሉ? ዳሩ ግን የአርባ ምንጭ ሰው ከሌላው ከተማ ነዋሪ ጋር እኩል የአ/ምንጭ ሙዝን በውድ ዋጋ እንደሚያገኝ ነው የሚታወቀው። ታድያ የዚህ የሙዝ ጉዳይ ልብ ሊባልለት አይገባም ትያለሽ? ሁሌም እንደሸፈተ እንዲኖር ልትፈቅጅለት አይገባም። አንቺ ግን እንድያው ዝም ብለሽ ሙዝ Export ታረጊያለሽ እንጂ ይሄ ነው የሚባል ጥቅም ስታገኚ አይተን አናውቅም። አይ 40_ምንጭ ፟ወይ ሙዝ ለራስሽ ጠግበሽ አትበይ፤ወይ ደግሞ በሙዝ ሽያጭ ገቢ ራስሽን አትጠግኚ!”
በሀገሪቱ የፍራፍሬ ገብያ ላይ የአንበሳውን ድርሻ የምትወስጂ መሆንሽን እና የፍራፍሬ አምራች መሆንሽን ዕውቅና ሰጥቶ አንድ የፍራፍሬ ማቀነባበርያ ፋብሪካ የገነባ አካል እንኳን የለም። ውይ የኔ ነገር፡ፋብሪካ አልኩ እንዴ? በጣም ይቅርታ፦ከአንድ በላይ ፋብሪካ እንዳይኖረን ተደርገን!
ለነገሩ ሙዝ አልኩ እንጂ ሌላኛው ያንቺ መገለጫ የሆነው የዓሣው ጉዳይም ተመሳሳይ ነው። አንድ የ7 ዓመት ታዳጊ ታናሽ ወንድሜ በቅርቡ በስልክ እንደነገረኝ ከሆነ ዓሣን የሚያውቀው በ3ኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ መጽሐፋቸው ላይ ካልሆነ በቀር እሱ የልጅነት ዕድሜውን እያሳለፈባት በሚገኘው ከተማ እንደልብ እንደሌለ በልጅ አንደበቱ ሲነግረኝ ድንቅ ነበር ያለኝ። እኔ እስከማውቅሽ ድረስ አንቺ ዓሣን ሳትሰስቺ ለልጆችሽ ትመግቢ ነበር።
በኳስ ጥበባቸው ድፍን ሀገርን ያስገርሙ የነበሩት ብርቅዬ የኳስ ከዋክብቶችሽ የጥንካሬያቸው እና የውጤታማነታቸው ሚስጥር ዓሣን እንደልባቸው እየተመገቡ ማደጋቸው እንደሆነ ሀገር ሁሉ የሚናገረው ጉዳይ ነው። ዛሬ ዛሬ የቀድሞው ባለታሪክ ክለብ( አርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ) አልጋ ወራሹ አ/ምንጭ ከነማ ተጫዋቾች ዓሣን እንደልብ ጠግበው ስለማይበሉ ይሁን አይሁን በውል ባይታወቅም በአንድ ትልቅ ውቅያኖስ ላይ በመጓዝ ላይ እያለች በተደጋጋሚ በሚነሳ የውሀ ማዕበል እንደምትናጥ መርከብ የሊጉን የዋንጫ ፉክክር መቋቋም አቅቶታል።ከነማ ሊጉን ከተቀላቀለበት ዓመት አንስቶ በነበሩት 4 ዓመታት የጨርቆችን ያክል ስኬታማ ጉዞ ባለማድረጉ እንደ የትኛውም ያንቺ ተዎላጅ ትንሽ ቅር ብሰኚም ሁሌም በድልም ሆነ በሽንፈት ጊዜ ከጎኑ በማይለዩት ጨዋ እና ስፖርት ወዳድ ህዝብሽ ግን ሁሌም ቢሆን እኮራለው።
እውነት ለማውራት አርባ ምንጭዬ፦ ሀገሩን እና ባህሉን ጠንቅቆ የምያውቅ ኩሩ ህዝብ አለሽ! የባህሉ እና የማንነቱ መገለጫ የሆነውን የባለ ቀይ፣ቢጫ እና ጥቁር ቀለማት አርማውን ዱንጉዛን ለብሶ የሚሰጠው የድጋፍ ስሜት የተለየ እና በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የማይገኝ ነው።
ስለዱንጉዛ ካነሳን አይቀር እንድያው ካላስቸገርኩሽ አርባ ምንጭዬ፡ አስተዳዳሪዎችሽን አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ! እንደምትይልኝ፥ ”ግን እስከመቼ ነው የኛው የራሳችን የሆነውን የዱንጉዛን የባለቤትነት ጉዳይ የማታስከብሩት?. . . . እስከመቼስ የጋሞ ወጣቶች ዱንጉዛን ለብሰው አንተ ጋሞ ነህ መባል ሲገባቸው የሌላ ብሄር ስም እየተጠራ ማንነታቸው የማይታወቅ እስኪመስላችው ድረስ እንፈቅዳለን?”
እኔ እስከማውቀው ድረስ በሀገራችን የሚገኙት ከ80 በላይ የሚሆኑት ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉም የየራሳቸው የሆነ ባህል፣ቋንቋ፣የአመጋገብ እና የአለባበስ ሥርዓት ወዘተ... አሏቸው። በዚህ መሰረትም ይሄ ባህላዊ ልብስ የኦሮሞ ነው፣የሲዳማ ነው፣የትግሬ ነው፣የአማራ ነው ወዘተ... እየተባለ ሲጠራ እንጂ ይሄ ባህላዊ አለባበስ የኦሮሞ እና የትግሬ ነው ወይም የሲዳማ እና የትግሬ ነው ሲባል ሰምቼም አይቼም አላውቅም። ምክንያቱም እያንዳንዳቸው የተለያዩ ብሄሮች ስለሆኑ የየራሳቸው መለያ አልባሳት አሏቸው።በተመሳሳይ ወንድማማች በሆኑት በወላይታ እና በጋሞ ብሄረሰቦች መካከል የባህል መቀራረብ ወይም መመሳሰል ሊኖር ይችል ይሆናል እንጂ ተመሳሳይ የባህላዊ ልብስ ሊኖራቸው ዘንድ የግድ አይደለም። ምክንያቱም ሁለቱም እራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ ብሄሮች ናቸውና!
እኔ የማይገባኝ ነገር ቢኖር ስለዱንጉዛ የባለቤትነት ጉዳይ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር የመንግስት ካድሬዎች “ዱንጉዛ የጋሞን እና የወላይታ ህዝቦችን የሚያስተሳስር ነው” እያሉ የሚሰጡት ማስተባበያ የሚመስለው መልሳቸው ነው። ስለዱንጉዛ ይሄን እና የመሳሰሉትን ነገሮች የመጠየቅ ህገ-መንግስታዊ መብት ያለው የጋሞ ብሄር ተወላጅ አሁንም እያለ የሚገኘው “ዱንጉዛ የጋሞ ስለሆነ ሌላው አይልበሰው ሳይሆን ተገቢ እና የ21ኛውን ክፍለ-ዘመን የሚመጥን ጥያቄ ነው!” “የዱንጉዛ የባለቤትነት ጉዳይ መልስ ሊሰጠው ይገባል!”
በቅርቡ የዱንጉዛ ጉዳይ መልስ ተሰጦት ወንድማማች የሆኑት የወላይታ እና የጋሞ ተወላጆች በፍቅር እንደሚለብሱት ተስፋ አደርጋለው!
በተረፈ አርባ ምንጭዬ፡ ባለሁበት ቦታ ሆኜ ጎሬቤቶችሽ እነ ሀዋሳ፣ሶዶ እና ሌሎችም እህት የሀገሪቱ ከተሞች የተሳፈሩበት የልማት ባቡር ከቆምሽበት ፌርማታ ድረስ መጥቶ እንዲወስድሽ እፀልያለው።
በቅርቡ ስመጣ አምረሽ እና ተውበሽ እንደምትጠብቂኝ ተስፋ አደርጋለሁ!
ፈጣሪ ሀሳብሽን እና ህልመሽን ሁሉ ያሳካልሽ! ሠላም ሁኚልኝ!
ያንቺው ልጅሽ ኪሩቤል ነኝ!

No comments:
Post a Comment