የምርጫ 2007 አሀዛዊ መረጃዎች በጋሞ ጎፋ ዞን
ጋሞ ጎፋ የጥበብ ምዕድር! Gamo Gofa , Land of Art! |
- በጋሞ ጎፋ ዞን ለመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠብቀው ህዝብ ከእቅዱ 10 በመቶ በበለጠ ተሳትፎ ከ657 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡
- እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡት ደኢህዴን/ኢህአዴግ፣ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያ ፖርቲ /ኢዴፖ/፣ ቅንጅት ለአድነትና ለዴሞክራሲ፣ ሰማያዊ ፖርቲ፣ መድረክ፣ አዲስ ትውልድ ፖርቲ፤የኢትዮጵያ ፍትህ እና ዴሞክራሲያዊ ኅይሎች /ኢፍዴኅ/ ፣የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅይሎች ናቸው፡፡
- ደኢህዴን/ኢህአዴግ 14 ለህዝብ ተወካዮችና 40 ለክልል ምክር ቤቶች ያቀረበ ሲሆን ኢዴፓ ሰባት ለህዝብ ተወካዮችና 11 እጩዎችን ደግሞ ለክልል ምክር ቤት አስመዝግበዋል።
- ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርት አምስት እጮችን ለተወካዮች ምክር ቤት 13 ደግሞ ለክልል ምክር ቤት ማስመዝገቡንና ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ስድስት ለተወካዮች እና 12 ለክልል ምክር ቤት አቅርቧል፡፡
- መድረክና አዲስ ትውልድ ፓርቲም እያንዳንዳቸው ሁለት ለህዝብ ተወካዮችና ስድስት ለክልል ምክር ቤት ስያስመዘግቡ አንድ የግል ተወዳዳሪም አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው ተመዝግበዋል።
- በዞኑ እስከ የካቲት 1 ቀን 2007 ዓ ም ድረስ በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ ከ657 ሺህ 201 በላይ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።
- በዞኑ በመራጭነት የተመዘገበው ህዝብ በአራተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር ሲነጻጸር ከ21 ከመቶ በላይ ብልጫ ያለው ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እቅድ መሰረት በዞኑ በዘንድሮ ምርጫ 590 ሺህ 786 መራጮች ይመዘገባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ህብረተሰቡ በመራጭነት ባሳየው ከፍተኛ ተሳትፎ ከእቅዱ 10 ከመቶ በላይ ሊሳካ ችሏል።
- በመራጭነት ከተመዘገቡት መካከል ከ314 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
No comments:
Post a Comment