Popular Posts

Wednesday, April 13, 2016

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ ክልል ሁለተኛ መዳረሻውን ሊከፍት ነው


     Ethiopian airline is about to kick off flights to its second destination in southern ethiopia,city of
      hawasa. There will be 4 flights within a week.


  70ኛ ዓመት ምሥረታውን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገሪቱ 20ኛ በደቡብ ክልል ደግሞ 2ኛውን መዳረሻ ሊከፍት መሆኑ ተዘግቧል። አየር መንገዱ በረራውን የሚጀምረው ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ሀዋሳ ነው።
በሀዋሳ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፍያ ግንባታ ሙሉበሙሉ ባይጠናቀቅም አየር መንገዱ በሳምንት 4 ቀናት ወደከተማይቱ ለመብረር መወሰኑን ነው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ለኢዜአ የገለጹት።

ላለፉት 10 ዓመታት በክልሉ በቸኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻ የነበረችው የአርባ ምንጭ ከተማ ነበረች።
አየር መንገዱ ወደ አርባ ምንጭ በየቀኑ ከማድረጉም ባለፈ ከተለያዩ  የውጭ ሀገራት ወደ ከተማይቱ የቀጥታ በረራም ይደረጋል።
ወደ ሀዋሳ የሚደረገው በረራ Q - 400 በተባለው አውሮፕላን ሲሆን  20ኛው የአገር ውስጥ መዳረሻው ትሆናለች።

በረራውም ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብና እሁድ እንደሚሆንም ኢዜአ  አየር መንገዱን ጠቅሶ ዘግቧል ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳሉት በረራው ለአገር ውስጥ መንገደኞች ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የመስጠት ጥረት የሚያጎለብት ነው።

የበረራው መጀመር በክልሉ በፍጥነት እያደገ በመጣው ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፍሰት ውስጥ ከአገር ውስጥም ሆነ ከመላው አለም ወደ ሀዋሳ የሚደረጉ ጉዞዎችን ያቀላጥፈዋልም ብለዋል።

No comments:

Post a Comment