Popular Posts

Wednesday, March 9, 2016

ሀገሪቱን ያጠቃው የኤልኒኖ ክስተት ያስከተለው በሽታ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሰው ህይወትን ቀጥፏል።

ሀገሪቱን ያጠቃው የ
ኤልኒኖ ክስተት ያስከተለው በሽታ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሰው ህይወትን ቀጥፏል።                                                         
በአርባ ምንጭ እና አካባቢዋ 
የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎ የተከሰተ የአጣዳፊ በሽታ በርካታ የሰው ህይወትን መቅጠፉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።


 በጋሞጎፋ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያና በአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም በሰገን ዞን አማሮ ወረዳ አካባቢ የአጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ መከሰቱን ይፋ ያደረገው የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ችግሩን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽብሩ አሠጋኸኝ እንደገለፁት የበሽታው መንስኤ ከኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ሰባት በሽታዎች አንዱ አተት መሆኑን አስታውሰው ችግሩ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
እንደ ሃላፊው ገለፃ በሽታውን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር ግብረሃል ተቋቋሞ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም በጋሞጎፋ ዞን በሁሉም ወረዳዎች ህብረተሰቡ የራሱንና የአካባቢውን ንፅህና መጠበቅ እንዳለበትና የበሽታውን ምልክት ሲያይ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መምጣት እንዳለበት በአካባቢ ቋንቋ ትምህርት በስፋት መሰጠቱን አክለው ገልፀዋል፡፡

ከበሽታው መከሰት ጋር በተያያዘ እስካሁን ሰዓት ድረስ አራት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡ በአርባምንጭ ዙሪያ በዘጊቲ ቀበሌ ሶስት ሰዎች በአርባምንጭ ከተማ በድል ፋና ቀበሌ አንድ ስው በድምሩ አራት ሰዎች እንደሆኑ ገልጸው ዘጠና ሁለት ሰዎች ታክመው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አቶ እንዳሻው አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment