የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድና ዲኤምሲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ለሁለት ቀናት ተቀብላ ያስተናገደችው አርባ ምንጭ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን ወደ ቤትዎ በሰላም መጡ››፣ ‹‹እንኳን ለከተማችን 50ኛ ዓመት አደረሰን›› የሚሉና የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ባነሮች በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ተሰቅለው ይታያሉ፡፡
ከተቆረቆረች ግማሽ ምዕታመት ያስቆጠረችው አርባ ምንጭ የ50ኛ ዓመት የልደት በዓልዋን በተለያዩ ክንውኖች ያከበረች ሲሆን፣ የበዓሉ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ደግሞ ባለፈው ነሐሴ 30 ቀንና ቅዳሜ ጳጉሜን 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ተከናውኗል፡፡
ከበዓሉ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም መካከል አንዱ አርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን የተገነባውና የአርባ ምንጭ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታን ያጠቃለለው የሁምቦ አርባ ምንጭ የምዕራፍ አንድ 75 ኪሎ ሜትር መንገድ የምረቃ ሥርዓት ነው፡፡
ለአርባ ምንጭና ለአካባቢው ነዋሪዎች የዓመታት ምኞት የነበረው ይህ የመንገድ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በይፋ ተመርቋል፡፡ መንገዱ ለዚህ ደረጃ መብቃቱ ለከተማው ነዋሪ የተለየ ስሜት የፈጠረ ነበር፡፡ ደስታቸውንም በአደባባይ ወጥተው ገልጿል፡፡ ወደ አርባ ምንጭ ለመግባት ወይም ከአርባ ምንጭ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ለመጓጓዝ እርጅና የተጫነው ከርካሳ መንገድና በኩልፎ ወንዝ ላይ የነበረው ድልድይ ከተማዋን ከአጠቃላይ እንቅስቃሴ የገታ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እንደገለጸው፣ አሁን በአስፓልት ደረጃ የተሠራው መንገድ ከ45 ዓመት በፊት በጠጠር የተሠራ መንገድ ሲሆን በአገልግሎት ብዛት ተጎድቶ የቆየ ነው፡፡ አርባ ምንጭ ከተቆረቆረች ከሦስት ዓመት በኋላ ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ሆነው የቆዩት አቶ ዘውዱ ጥላሁን እንደሚሉት፣ በኩልፎ ወንዝ ለመሻገር የነበረው ፈተና ቀላል አልነበረም፡፡ በመንገዱ መጎዳት ምክንያት ተሽከርካሪዎች ወደዚህ አካባቢ እንደልብ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ በዕለቱ የተመረቀው የ75 ኪሎ ሜትር መንገድ ከመሠራቱ በፊትም የነበረው መንገድ አርባ ምንጭን ወደኋላ ያስቀረ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘውዱ፣ ይህ ታሪክ የሚለወጥ ስለመሆኑ ይናገራሉ፡፡
የዚህ መንገድ ግንባታ መጠናቀቅ የተለየ ስሜት እንዳሳደረባቸው ከገለጹት መካከል አንዱ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ናቸው፡፡ በምርቃት ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹትም፣ ‹‹የከተማዋን 50ኛ ዓመት እያከበርን ባለንበት ወቅት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ የከተማችን ቁልፍ ችግር የሆነውን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በመፈጸም በአርባ ምንጭ ከተማ ታሪክ በአጭር ጊዜ ትልቅ ድልድይ ተገንብቶ ተረክበናል፡፡ ከተማዋን ለሁለት የከፈለውን ወንዝ በማገናኘት በይፋ የተመረቀውን ድልድይ የከተማችን የልደት በዓልዋ ስጦታ አድርገን የምንወስደውም ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የከተማዋን አስፓልት ሥራ ሌት ተቀን በመሠራታቸው የዲኤምሲን ባለቤት አቶ ዳንኤል ማሞን፣ የኩባንያውን ሠራተኞችና አማካሪ መሀንዲስን አመስግነዋል፡፡
በዲኤምኤስ ኮንስትራክሽን የተገነባው ይህ መንገድ በከተሞች አካባቢ 27 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአነስተኛ ከተሞች ደግሞ 19 ሜትር ስፋት ኖሮት የተሠራ ነው፡፡ ከ825.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪም ጠይቋል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ የተጀመረው በብላቴ ወንዝ ድልድይ ሲሆን፣ በአርባ ምንጭ ከተማ በምትገኘው በኩልፎ ወንዝ ድልድይ የሚያበቃ ነው፡፡ የኩልፎ ወንዝ ድልድይም 62 ሜትር ርዝመትና 28.6 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰቀላንና የሰቻ ከተሞችን ያገናኛል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ የሦስት አደባባዮች ግንባታም የዚሁ ፕሮጀክት አካሎች ናቸው፡፡
የዚህ መንገድ ግንባታ ለዚህ ደረጃ ይብቃ እንጂ መንገዱ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ያለመጠናቀቁ የአካባቢውን ነዋሪዎች ያስቆጣ ነበር፡፡ አቶ ዘውዱ እንደገለጹትም፣ የመንገዱ የግንባታ ሥራ በመሀል ላይ መቋረጡ የከተማውን ነዋሪ ተስፋ እስከማስቆረጥና ለአቤቱታም ወደ መንግሥት አካላት ቀርቦ ነበር፡፡ አሁን ግን ያ ሥጋት ቀርቶ አያልቅ ይሆን ተብሎ የነበረው መንገድ ቃል በተገባው መሠረት እውን መሆኑ እርሳቸውንም ሆነ የከተማዋን ነዋሪ አስደስቷል ብለዋል፡፡ በተለይ መንገዱ ለምን እንደተጓተተ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና ከአስተዳደሩ ከተሰጠው ማብራሪያ ሌላ ኮንትራክተሩ መንገዱን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀው እንደሚያስረክቡ በገቡት ቃል መሠረት መፈጸማቸው እጅግ ያስደሰታቸው ስለመሆኑም አቶ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡ ከዋናው መንገድ ሌላ የከተማው የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ በተገባው ቃል መሠረት ተሠርቷል፡፡ ጥቃቅን የሚባል ቀሪ ሥራዎችንም ለማጠናቀቅ ቀን ተሌት እየተሠራ ሲሆን፣ የመንገዱ ግንባታው የከተማዋን ገጽታ መቀየር ችሏል፡፡
ዲኤምሲ የዚህን መንገድ ፕሮጀክት ሲረከብ የፕሮጀክቱ ግንባታ 106 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ቢኖረውም፣ በዕለቱ ግንባታው ተጠናቅቆ የተመረቀው ግን 75 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ቀሪው 31 ኪሎ ሜትር መንገድ ለብቻው ተነጥሎ እንደ አዲስ ፕሮጀክት እንዲሠራ ተደርጓል፡፡ ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት ነበረው፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹትም፣ ለመንገድ ፕሮጀክቱ መዘግየት ዋነኛ ተደርጎ የተወሰደው በግንባታ ወቅት በፕሮጀክቱ የተለያዩ ቦታዎች ያጋጠሙ ችግሮችና በጥቅሉ 31 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የፕሮጀክቱ ክፍል እንደ አዲስ መሠራት ስለነበረበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደገለጹትም፣ 31 ኪሎ ሜትሩ መንገድ ችግር የፈጠረው ቀደም ብሎ በተሠራው ዲዛይንና የግንባታ ደረጃ ሊሠራ ባለመቻሉና የዲዛይን ለውጥ በማስፈለጉ ነው፡፡ አጠቃላይ የሁምቦ አርባ ምንጭ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጠናቀቅ የነበረበት በ2004 ዓ.ም. ነበር፡፡ ሆኖም በግንባታ ወቅት በተለያየ ቦታ 31 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ዲዛይን እንደገና እንዲሠራ ማስገደዱ ደግሞ የፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ እንዲቋረጥ እስከማድረስ ደርሶ ነበር፡፡ ለፕሮጀክቱም ሥራ ትልቅ ፈተና ነበር፡፡ ይህ ክፍል ተነጥሎ እንዲወጣ ተደርጎ ቀሪው 75 ኪሎ ሜትር መንገዱ እንደ ምዕራፍ አንድ ሥራ ተወስዶ ቀሪው 31 ኪሎ ሜትር መንገድ ደግሞ እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮጀክት ተወስዶ እንዲሠራ ሊወሰን ችሏል፡፡ በዚህ ውሳኔ መሠረት አዲስ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ በዚህም ጨረታ ዲኤምሲ አሸናፊ ሆኖ ሥራውን ተረክቦ ግንባታውን በማከናወን ላይ ነው፡፡
እንደ አቶ ሳምሶን ገለጻ በዚህ ጨረታ አምስት ተቋራጮች ተወዳድረው ነበር፡፡ እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ ለተቆጠረው ለ31 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በወጣው ጨረታ ዲኤምሲ አሸናፊ የሆነበት ዋጋ በ700.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ በአዲሱ ውል መሠረት የሁለተኛው ምዕራፍ መንገድ ግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከ2007 ዓ.ም. አጋማሽ በኋላ ይሆናል ተብሏል፡፡
የሁምቦ አርባ ምንጭ አስፋልት መንገድ የሁለተኛው ምዕራፍ 31 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ ርዝመታቸው እስከ 80 ሜትርና 19 ሜትር ስፋት ያላቸው የሁለት ትላልቅ ድልድዮች ግንባታ ሥራዎችን አካቶ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመንገዱ ግንባታ ከ51 በመቶ በላይ የተከናወነ ሲሆን፣ 130 የሚሆኑ የውኃ መተላለፊያ መስመሮች ግንባታን በማካተት የአዲስ ቴክኖሎጂና አሠራር ዘዴንም በመጠቀም ግንባታው እየተፋጠነና በሚቀጥሉት ጥቂት ወራትም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለዚህ በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው መንገድም ከ700.4 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግሥት ተመድቧል፡፡
የ75 ኪሎ ሜትር መንገድ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ የዚህ መንገድ ግንባታ መጠናቀቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አለው፡፡ ‹‹የአርባ ምንጭና አካባቢው በአገሪቱ ትልቅ ሀብት ያለበት ተብሎ የሚወሰድ ቦታ ነው፡፡ የቱሪዝም ሀብቱ ተዝቆ የማያልቅ ነው፡፡ ስለዚህ ቱሪስቶች በሰላምና በተመቻቸ ሁኔታ እንዲጓዙ ካስፈለገ መሠረተ ልማት በጣም ወሳኝ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የአርባ ምንጭ አካባቢ በፌዴራል መንግሥት የሆርቲካልቸር ክላስተር ተብሎ የተመረጠ በመሆኑ ወደፊት የአግሮ ፕሮስሲንግና አበባን ጨምሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የሚካሄዱበት አካባቢ እንደሚሆን የጠቀሱት አቶ ኃይለ ማርያም፣ እንዲህ ዓይነቱን ዕቅድ ለማስፈጸም እንዲህ ዓይነት መሠረተ ልማቶች የግድ ማስፈለጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የአርባ ምንጭ የአውሮፕላን ማረፊያን መሠረት አድርጎ በቀጥታ ዓለም አቀፍ በረራ የሚኖርበት ዕድል ስለመኖሩም የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ባለሀብቶች እዚህ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ካስፈለገ መሠረተ ልማት የግድ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹አርባ ምንጭ ከፍተኛ የሙዝ ምርት በማምረት የሚታወቅ ነው፡፡ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሙዝ ከአርባ ምንጭ ይጫናል፡፡ ለዚህ ምርት የሚሆን የተሻለ መንገድ መኖር ስላለበት እንዲሁም ለአጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚ ልማት አሁን የተሠራው መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፤›› ብለዋል፡፡ በዕለቱ የተመረቀው መንገድ የቱሪስት መናኸሪያነታችንም ከፍ የሚያደርግ ነውና የመንገድ ግንባታው ተጠናቅቆ ሥራ መጀመሩ በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
በአገሪቱ የተቋራጮች የብቃት ደረጃን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ ‹‹የአገራችን ተቋራጮች በኮንክሪት አስፓልት መንገድ ላይ የተሻለ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹በእርግጥ በየጊዜው ውጣ ውረዶች አሉ፡፡ አሁን እንደሚታየው ጠንክረው ከወጡ ወደፊት የአገሪቱን የመሠረተ ልማት ግንባታና ትልልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችንም ጭምር አገራዊ ተቋራጮች ሊይዙ እንደሚችሉ በትክክል ምልክቶች እየታዩ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ግን መንግሥትም ደግፏቸው አቅማቸው የበለጠ መጎልበት እንዲችል ማድረግ አለብን ያሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ አሁንም ቢሆን ግን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ዕውቀት ችግርን አልተሻገሩም ብለዋል፡፡ ስለዚህ መኩራራት እንደማያስፈልግና የዓለምን የመጨረሻ እስክንደርስ ድረስ መሻሻሎች መኖር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የአገር በቀል ኮንትራክተሮች ጥሩ እየሄዱ ቢሆንም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንቱ መሻሻል ይኖርበታል፡፡ የሁምቦ አርባ ምንጭም ፕሮጀክት ከጊዜ አንፃር ሲታይ የተወሰነ መዘግየት መታየቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንዲህ ዓይነት መዘግየቶች በማስወገድ አቅማቸውን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል፡፡ ‹‹አሁን ኮንትራክተሩ (ዲኤምሲ) ራሱን አሻሽሎ ሪስትራክቸር አድርጎ በመግባቱ የተሻለ ሥራ ሠርቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ተምሮ ሌሎችም ኮንትራክተሮች የበለጠ ውስጣቸውን እንዲፈትሹ መንግሥትም የአቅም ግንባታ ሥራን ማጠናከር ይገባናል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው ደግሞ የመንገድ ፕሮጀክቱ በቱሪስት መስህብነት የምትታወቀውን የአርባ ምንጭ ከተማን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በደቡብ ክልል የሚገኙ ሦስት ዞኖችንና አንድ ልዩ ወረዳን ማለትም የከምባታ ጠምባሮ፣ የጋሞ ጎፋና የወላይታ ዞኖችንና የአላባ ልዩ ወረዳን እርስ በርስ የሚያገናኝ ጭምር ነው፡፡ መንገዱ ከሞጆ ተገንጥሎ እስከ ጎረቤት አገር ኬንያ ድረስ የሚዘልቅ ዋና መንገድ አካል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያን ክፍል ከሌሎች ጋር ለማገናኘትና ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑን የሚገልጸው የባለሥልጣኑ መረጃ ይህም ጊዜን፣ ገንዘብንና እንግልትን በእጅጉ እንዲቀንስ ያስችላል ብሏል፡፡
10 September 2014 ተጻፈ በ ዳዊት ታዬ[reporter ጋዜጣ]

No comments:
Post a Comment