Popular Posts

Wednesday, April 13, 2016

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ ክልል ሁለተኛ መዳረሻውን ሊከፍት ነው


     Ethiopian airline is about to kick off flights to its second destination in southern ethiopia,city of
      hawasa. There will be 4 flights within a week.


  70ኛ ዓመት ምሥረታውን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገሪቱ 20ኛ በደቡብ ክልል ደግሞ 2ኛውን መዳረሻ ሊከፍት መሆኑ ተዘግቧል። አየር መንገዱ በረራውን የሚጀምረው ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ሀዋሳ ነው።
በሀዋሳ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፍያ ግንባታ ሙሉበሙሉ ባይጠናቀቅም አየር መንገዱ በሳምንት 4 ቀናት ወደከተማይቱ ለመብረር መወሰኑን ነው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ለኢዜአ የገለጹት።

ላለፉት 10 ዓመታት በክልሉ በቸኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻ የነበረችው የአርባ ምንጭ ከተማ ነበረች።
አየር መንገዱ ወደ አርባ ምንጭ በየቀኑ ከማድረጉም ባለፈ ከተለያዩ  የውጭ ሀገራት ወደ ከተማይቱ የቀጥታ በረራም ይደረጋል።
ወደ ሀዋሳ የሚደረገው በረራ Q - 400 በተባለው አውሮፕላን ሲሆን  20ኛው የአገር ውስጥ መዳረሻው ትሆናለች።

በረራውም ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብና እሁድ እንደሚሆንም ኢዜአ  አየር መንገዱን ጠቅሶ ዘግቧል ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳሉት በረራው ለአገር ውስጥ መንገደኞች ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የመስጠት ጥረት የሚያጎለብት ነው።

የበረራው መጀመር በክልሉ በፍጥነት እያደገ በመጣው ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፍሰት ውስጥ ከአገር ውስጥም ሆነ ከመላው አለም ወደ ሀዋሳ የሚደረጉ ጉዞዎችን ያቀላጥፈዋልም ብለዋል።

Friday, March 11, 2016

Best pics of the month/የወሩ ምርጥ ፎቶዎች

"ጋሞ ጎፋ"- የጥበብ እና የዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት መገኛ ምዕድር
እግዜር በኪነጥበቡ ውብ አድርጎ የሰራት ከተማ - አርባ ምንጭ



























"ጋሞ ጎፋ"- የጥበብ እና የዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት መገኛ ምዕድር

Wednesday, March 9, 2016

ሀገሪቱን ያጠቃው የኤልኒኖ ክስተት ያስከተለው በሽታ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሰው ህይወትን ቀጥፏል።

ሀገሪቱን ያጠቃው የ
ኤልኒኖ ክስተት ያስከተለው በሽታ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሰው ህይወትን ቀጥፏል።                                                         
በአርባ ምንጭ እና አካባቢዋ 
የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎ የተከሰተ የአጣዳፊ በሽታ በርካታ የሰው ህይወትን መቅጠፉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።


 በጋሞጎፋ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያና በአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም በሰገን ዞን አማሮ ወረዳ አካባቢ የአጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ መከሰቱን ይፋ ያደረገው የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ችግሩን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽብሩ አሠጋኸኝ እንደገለፁት የበሽታው መንስኤ ከኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ሰባት በሽታዎች አንዱ አተት መሆኑን አስታውሰው ችግሩ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
እንደ ሃላፊው ገለፃ በሽታውን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር ግብረሃል ተቋቋሞ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም በጋሞጎፋ ዞን በሁሉም ወረዳዎች ህብረተሰቡ የራሱንና የአካባቢውን ንፅህና መጠበቅ እንዳለበትና የበሽታውን ምልክት ሲያይ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መምጣት እንዳለበት በአካባቢ ቋንቋ ትምህርት በስፋት መሰጠቱን አክለው ገልፀዋል፡፡

ከበሽታው መከሰት ጋር በተያያዘ እስካሁን ሰዓት ድረስ አራት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡ በአርባምንጭ ዙሪያ በዘጊቲ ቀበሌ ሶስት ሰዎች በአርባምንጭ ከተማ በድል ፋና ቀበሌ አንድ ስው በድምሩ አራት ሰዎች እንደሆኑ ገልጸው ዘጠና ሁለት ሰዎች ታክመው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አቶ እንዳሻው አስረድተዋል፡፡

Thursday, May 21, 2015

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል ደኢህዴን/ኢህአዴግን ወክለው ለፓርላማ ይወዳደራሉ

በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሀገርአቀፍ ምርጫ በጋሞ ጎፋ ዞን በሚገኙ የምርጫ ክልሎች የገጂው ፓርቲ ዕጩዎች ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር ብርቱ ትግል ያደርጋሉ                                                                               የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል ደኢህዴን/ኢህአዴግን ወክለው ለፓርላማ ይወዳደራሉ            በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር ድኤታ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ መምርያ ሀላፊ የነበሩት አቶ ታገሰ ጫፎ በመጪው እሁድ በሀገሪቱ ታሪክ ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ገጂው ፓርቲን ወክለው በአርባ ምንጭ የምርጫ ክልል የህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤትን ወንበር ለማግኘት ይፎካከራሉ። 
አቶ ታገሰ በዝህ የምርጫ ክልል ድልን የሚቀናጁ ከሆነ እና መንግስትም አብላጫውን ድምፅ በማግኘት ካሸነፈ በአቶ ሀይለማርያም የድህረ-ምርጫ የካቢኔ ሹም ሸረት ውስጥ የሚኒስትርነት ቦታን ሊቆናጠጡ ይችላሉ ተብሏል።ይሄም የሚሆን ከሆነ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የጋሞ ብሄር ተዎላጅ በሀገሪቱ የከፍተኛ የሥልጣን ዕርከን ውስጥ የሚገባ ይሆናል።በተጨማሪም በዚሁ የምርጫ ክልል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ደኢህዴን በመወከል ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ይወዳደራሉ። በዘንድሮው ምርጫ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብዛት ለፉክክር ከቀረቡባቸው የምርጫ አካባቢዎች እና በገጂውም ሆነ በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ አንድ ጠንካራ የፖለቲካ ይዞታ በምትቆጠረው የጋሞ ጎፋ ዞን አጓጊ ፉክክር ይጠበቃል። በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ አንድነት መድረክ /መድረክ/ ለኢህአዴግ መራሹ ገጂ ፓርቲ ትልቅ ፈተና ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። ለአብነት እንኳን ከሰሞኑ የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ አንድነት መድረክ የውጪ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር መራራ ጉዲና ፓርቲያቸው ድል እንደሚቀናጅ ከሚጠብቁት 5 አካባቢዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ዞን አንዷ እንደሆነች ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርባ ምንጭ ትሪቡን ድህረ-ገፅ ዘጋቢ አንዳንድ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሮ በላከልን ዘገባ መሠረት ምርጫው ሠላማዊ እና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።  በምርጫው ዋዜማ ለከተማዋ ህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበው በተገዙ ሁለት የከተማ አውቶቢሶች መደሰታቸውንም ተናግረዋል። ይሁንእና ግን በርካታ የባጃጅ ሹፌሮች ከሰሞኑ ተገዝተው በመጡት ሁለት የቢሾፍቱ ባሶች ከገበያ ውጪ እንሆናለን በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።

Wednesday, April 15, 2015

ምርጫ 2007 ዝግጅት በጋሞ ጎፋ ዞን ምን ይመስላል?


                የምርጫ 2007 አሀዛዊ መረጃዎች በጋሞ ጎፋ ዞን

ጋሞ ጎፋ የጥበብ ምዕድር! Gamo Gofa , Land of Art!
  • በጋሞ ጎፋ ዞን ለመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠብቀው ህዝብ ከእቅዱ  10 በመቶ በበለጠ ተሳትፎ 657 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡
  • እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡት ደኢህዴን/ኢህአዴግ፣ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያ ፖርቲ /ኢዴፖ/ ቅንጅት ለአድነትና ለዴሞክራሲ፣ ሰማያዊ ፖርቲ፣ መድረክ፣ አዲስ ትውልድ ፖርቲ፤የኢት ፍትህ እና ዴሞክራሲያዊ ኅይሎች /ኢፍዴኅ/ ፣የኢት ዴሞክራሲያዊ ኅይሎች ናቸው፡፡
  •  ደኢህዴን/ኢህአዴግ 14 ለህዝብ ተወካዮችና 40 ለክልል ምክር ቤቶች ያቀረበ ሲሆን ኢዴፓ  ሰባት ለህዝብ ተወካዮችና 11 እጩዎችን ደግሞ ለክልል ምክር ቤት  አስመዝግበዋል
  • ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርት አምስት እጮችን ለተወካዮች ምክር ቤት 13 ደግሞ ለክልል ምክር ቤት ማስመዝገቡንና ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ስድስት ለተወካዮች እና 12 ለክልል ምክር ቤት  አቅርቧል፡፡
  • መድረክና አዲስ ትውልድ ፓርቲም እያንዳንዳቸው ሁለት ለህዝብ ተወካዮችና ስድስት ለክልል ምክር ቤት  ስያስመዘግቡ አንድ የግል ተወዳዳሪም አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው  ተመዝግበዋል
  •  በዞኑ እስከ የካቲት 1 ቀን 2007 ድረስ በተካሄደው  የመራጮች ምዝገባ 657 ሺህ 201 በላይ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።
  • በዞኑ በመራጭነት የተመዘገበው ህዝብ በአራተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር ሲነጻጸር  21 ከመቶ በላይ ብልጫ ያለው ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እቅድ መሰረት በዞኑ በዘንድሮ ምርጫ 590 ሺህ 786 መራጮች ይመዘገባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ህብረተሰቡ በመራጭነት ባሳየው ከፍተኛ ተሳትፎ ከእቅዱ 10 ከመቶ በላይ ሊሳካ ችሏል።
  • በመራጭነት ከተመዘገቡት መካከል 314 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

በአባያና ጫሞ ሐይቅ ያለውን የአሳ ሀብት ደህንነት ለመጠበቅ የጋራ ስራ ያስፈልጋል

ከአባያና ጫሞ ሐይቅ የሚገኘውን የዓሳ ምርት ለማሳደግ በሐይቆቹ ደህንነት ላይ የሚሰሩ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የጋሞ ጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ። ባለፉት ስምንት ወራት ማህበራትና አርሶ አደሮች ካቀረቡት ሁለት ሺህ 571 ቶን የዓሣ ምርት ከ115 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ መገኘቱን ገልጿል።
 የዙኑ ግብርና መምሪያ የእንስሳት እርባታና መኖ ልማት የስራ ሂደት ተወካይ አቶ አቶ አንተነህ ጌታቸው ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ከሐይቆቹ የሚመርተውን የዓሳ ምርት መጠንና ጥራት ለመጨመር የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ዘንድሮ የተገኘው ምርት ካለፈው አመት ከ50 ቶን በላይ ብልጫ ቢኖረውም የሐይቆቹ የማምረት አቅም ከአምስት አመታት በፊት ከሚመረተው ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው በጣም ቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ችግሩ የሐይቆቹ ደህንነት በአግባቡ እየተጠበቀ አለመሆን፣በሐይቆቹ ዙሪያ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለሆነ ነው ብለዋል።
 በስምጥ ሸለቆ በዓሳ ምርት ክምችት የሚታውቀው የጫሞ ሐይቅ ብቻውን በዓመት ከ45 ሺህ ቶን በላይ፣አባያ ሐይቅ ደግሞ 3 ሺህ 500 ቶን ዓሣ የማምረት አቅም እንዳላቸውም ገልጸዋል። በተለይ በምርት ክምችቱ የሚታውቀው ጫሞ ሐይቅ በህገ ወጥ ዓሳ አስጋሪዎች መጨናነቁና ህገ ወጥ እርሻ መስፋፋት በአሳ ጫጩቶችና ዝሪያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል።
 ሐይቆቹን ከደለል በመከላከል የውሀ መጠኑን ለመጨመር በጋሞ ከፍተኛ አከባቢ በተከናወነው ተፋሰስ ልማት ሐይቆችን የሚመገቡ ገባር ወንዞች መጠን ቢጨምርም የሐይቆቹ ዙሪያ ወሰን ባለመከለሉ ህገ ወጥ አስጋሪነትን መከላከል ካልተቻለ በተፋሰስ ልማት ብቻ ውጤታማ እንደማይሆን ገልጸዋል።
 በአርባምንጭ ከተማ የዓሣ ምርት ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ይመረታል የተባለው ዓሣ በከተማው የግብይት ማዕከላት ስለማይቀርብ መጠቀም እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የሸቻ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አባቡ መላኩ እንደተናገሩት አርባምንጭና አካባቢው ቀደም ሲል በዓሳ ምርት ቢታወቅም ጥራት ያለው ዓሳ የሚሸጥበት የግብይት ማዕከል እንደሌለ አስታውቀዋል። “የዓሳ ግብይቱ በአምራቾችና ንግድ ቤቶች እንዲተሳሰሩ ተደርጓል፣ ንግድ ቤቶቹም በአንድ ከተማ ውስጥ የሚሸጡበት ዋጋ የተለያየ ነው፣ ዓሣ በብዛት እየተመረተ ለስጋ ሉካንዳ ቤት እንደሚከፈት ለዓሣ መሸጫ ቦታ ለምን አይመቻችም ” ሲሉ ጠይቀዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ማሞ በአሁኑ ወቅት አሳን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ ገልጸው ምሽት ላይ በኮንትሮባንድ ካልሆነ በቀር ዓሳ የሚገዙበት ህጋዊ ማዕከል እንደሌለ አስታውቀዋል።
ሆሎች፣ንግድ ቤቶችና ዓሣ ከአምራች የሚረከቡ ግለሰብ ነጋዴዎች ምርቱን ወጥ በሆነ ዋጋ እንደማይሸጡ አስታውቀው ለህብረተሰቡ ግን በህጋዊ መንገድ የሚሸጡ የጅምላና ችርቻሮ መሸጫ ቦታዎች መመቻቸት እንደሚገባ ገልጸዋል። የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ እልፍነሽ ያፖ ህገ ወጥ አሣ አስጋሪዎችን ለመከላከል ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የሐቆቹንን መጨናነቅ ለመከላከል እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ወራት በዓሳ ምርት በተሰማሩ ማህበራትና አርሶ አደሮች ሁለት ሺህ 571 ቶን የዓሳ ምርት ለገበያ በማቅረብ ከ115 ሚሊዮን 695 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በህጋዊ ዓሳ አስጋሪ፣አቅራቢና ችርቻሮ ላይ በተሰማሩ ከስምንት በሚበልጡ ህብረት ስራ ማህበራትና ከ40 የሚበልጡ የግል ሰራተኞች ከ15 በላይ ቸርቻሪዎችና ንግድ ቤቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአከባቢው ተጠቃሚ ምርቱን የሚያገኝበት ዘመናዊ የግብይት ማዕከል ከመፍጠር አንጻር ክፍተቶች እንዳሉ አስታውቀው በአርባምንጭ ከተማ የችርቻሮ ሱቆችን ለማስፋፋት ጥናት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ከአስተዳደርና ንግድ እንዱስትሪ ተቋማት እውቅና ውጭ በህገ ወጥ መንገድ ዓሳ ለማስገር የተሰማሩ ከ200 የሚበልጥ መረቦችን በመለየት እንዲቃጠል ማድረጉን ገልጸዋል።
የሐይቆቹን ደህንነት ለማስጠበቅ የዞን፣የወረዳና ቀበሌ መዋቅር፣ በዓሳ መምረትና ማጓጓዝ ስራ ላይ የተሰማሩ አካላትና አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑንም ወይዘሮ እልፍነሽ አስታውቀዋል።

ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየሰራን ነው-የጋሞጎፋ ዞን የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

በጋሞጎፋ ዞን 5ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ ፣ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑን የዞኑ የጋራ ምክር ቤት አባል ፓርቲዎች አስታወቁ።
  የምክር ቤቱ የወቅቱ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢፍዴኃግ) የጋሞጎፋ ዞን ኃላፊ አቶ ገዛህኝ ገለቱ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በዞኑ በፓርቲዎች የተቋቋመው የጋራ ምክር ቤት በምርጫ ሂደት የሚያጋጥመውን ችግር በውይይት እየፈታ ነው።
 በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በስሌና ኤልጎ ቀበሌ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢዴኃግ) አባላት ላይ ተፈጸመ የተባለውን በደል ምክር ቤቱ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ ቦታው ድረስ በመሄድ ማጣራቱን ገልጸዋል። ደኢህዴን/ኢህአዴግ የኢፍዴኃግ ፓርቲ አባላትን በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት አስሯል በሚል ያቀረበው አቤቱታ ትክክል አለመሆኑን በአጣሪ ኮሚቴው በኩል ተጣርቶ ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንዲታረም መደረጉን አስታውቀዋል።
 የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ሊቀመንበር አቶ ስጦታው ፓላ በምርጫው ሂደት የፓርቲ አባላት፣ደጋፊዎችና እጩ ተወዳዳሪዎች በፈለጉት መንገድ ተንቀሳቅሰው ፖስተር በመለጠፍ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በምርጫ ቅስቀሳው ሂደት ማንም በማንም ላይ የምርጫ ህጉን የሚጻረር ተግባር እንዳይፈጽም በጋራ ምክር ቤቱ አማካኝነት አቅጣጫ በማስቀመጥ የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ እየፈቱ መሆኑን አስታውቀዋል።
ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ነጻ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በምርጫ ህጉ ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረጋቸው እስካሁን የጎላ ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል። የምክር ቤቱ ኮሚቴ ሰብሳቢና የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን/ኢህአዴግ የገጠር ፓለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጋራ ምክር ቤት አባል ፓርቲዎች እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በዞኑ በቁጫና ዲታ ወረዳ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ ችግር ገጥሞኛል በሚል ኢፍዴኀግ ያቀረበውን አቤቱታ እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚቴ ቦታው ላይ ተገኝቶ ተፈጠረ የተባለውን ጉዳይ በማጣራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በጋሞ ጎፋ ዞን ደኢህዴን/ኢህአዴግ፣ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችና አዲስ ትውልድ ፓርቲ የምክር ቤቱ አባል ናቸው።