arba minch city is among a colliders the ethiopian government wants for horticulture development.
beggining to next year the government will invest millions of dollars on the chosen colliders.
The Ethiopian News Agency reports; በሃገሪቱ ለሆልቲካልቸር ግብርና ልማት ተስማሚ የሆኑ አምስት የልማት ኮሪደሮች መመረጣቸዉን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ጀኔራል ዶክተር ፈንታሁን መንግስቱ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት የልማት ኮሪደሮች የተመረጡት ዘርፉ ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት እያበረከተ ያለዉን አስተዋፅኦ የበለጠ ለማሳደግ ታስቦ ነው፡፡
የልማት ኮሪደሮቹ አዲስ አበባ-ኦሮሚያ፣ ሃዋሳ- አርባ ምንጭ፣ አዋሽ-ድሬዳዋና ሃረር፣ ባህርዳር- የአባይ ሸለቆና ደቡብ ጎንደር እንዲሁም መቀሌ- ራያና አላማጣ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
የልማት ኮሪደሮቹ የተመረጡት ለዘርፉ ያላቸዉ ምቹ ስነምህዳር፣ የአየር ትራንስፖርትን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማት መስፋፋት እንዲሁም ለወጭ ንግድ ያላቸውን ቅርበት መነሻ በማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በእነዚሁ የልማት ኮሪደሮች አበባና ቡናን ጨምሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የሚውል 50 ሺ ሄክታር መሬት የተለየ ሲሆን በልማቱ የሚሳተፉ አርሶ አደሮች ቁጥር ሲጨመር የሚለማዉ መሬትም እንዲሁ ይጨምራል ብለዋል፡፡
በሃገሪቱ ያለዉ የሰዉ ሃይልና በመካከለኛዉ ምስራቅና በአዉሮፓ ሃገሮች ሰፊ የገበያ እድል መኖር ለልማቱ ምቹ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ወደ ደቡብ አሜሪካ፣ ጃፓንና አፍሪካ ሃገራት ተጨማሪ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አርሶ አደሩ ምርቱን በአይነትም ሆነ በጥራት በማሳደግ ለፍጆታ ከማምረት አልፎ በገበያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸዉን ምርቶች ወደ ማምረት እየተሸጋገረ ሲሆን ዘርፉ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በማሳተፍ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ ሽግግሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣዉ በመስኖ የማልማት ባህል፣ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች የመሰረተ ልማት መስፋፋት የህብረተሰቡ ገቢ ማደግ ጋር ተያይዞ የአመጋገብ ባህል እየተቀየረ መምጣቱ እና ተያያዥ ሁኔታዎች ለዘርፉ መጎልበት ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውንም ገልፀዋል፡፡
በተለይ አነስተኛ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ማንጎ፣ ሙዝና ብርቱካን ጨምሮ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬ በጥራትና በብዛት በማምረት በጂቡቲ፣ ሱማሌና ደቡብ ሱዳን ሃገራት ያለውን የገበያ ፍላጎት በማሟላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/2030-2015-02-15-22-08-04#sthash.kAkKqCQt.dpuf